Skip navigation.

exploreopera

| Help

Sign up | Help

ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

ኢጣሊያ ሚላኖ

ከአዳም ነው ግኝትህ

ከአዳም ነው ግኝትህ
ዘፍ 1፡ 26- 28


ብዙ አውቀናል ስንል ብዙ ተምረናል፣
የጎደለን አለ ገና ይቀረናል፡፡
አንድ የመሆን ነገር እንደ ሻማ ቀልጦ፣
መስማማት ከበደን ከፍቅር ዘር በልጦ፡፡
ብዙና ተባዙ ምድርን ሙሏት ማለት፣
ተዋጉ አልነበረም ይህን እወቅ ፍጥረት፡፡
በሰናኦር ምድር ቋንቋ ቢደባለቅ፣
“ባቢሎን” ተብሎ ከተማ ቢታወቅ፣
ምድሪቱን ቢሞላት ህዝብ ተበትኖ፣
ሃገር ቢከፋፈል ድንበር ተወስኖ፣
ለምን ነው መንደዱ የጸብ የጥል እሳት፣
የሰው ልጅ ለማጥፋት ጦር መምዘዝ ጦር ማንሳት፡፡
ምነው ያዜብ ንግስት ከጦቢያ ተነስታ፣
ሰላም ይዛ መጣች እውቀት ጥበብ አይታ፡፡
የጀግና ዘር ብለህ አትታጠቅ ዝናር፣
መግደል ውርስ አይሆንም እባክህ ሰው ተማር፡፡
ባለንበት ዘመን ጀግንነት ወንድነት፣
ተስማምቶ መኖር ነው በፍቅር ባንድነት፡፡
የሰው ልጅ ከማዳን የሰው ልጅ ለማጥፋት፣
ስንት ጥበበኛ ይጫወታል በእሳት፡፡
ሰው ጥበብ እውቀትህ ችሎታህ ሲለካ፣
ሃብት ያፈሰስክበት ለጥይት ነው ለካ፡፡
በደቂቃ የሚገል መሳሪያ ሲሰራ፣
በደቂቃ የሚድን ምነው አልተሰራ?
ባልተገባ ነገር በማይሆን ተጣልተን፣
አብረን እየበላን ሆድና ጀርባ ነን፡፡
መንገድ ሊያሳስተን ሊያጣላን ከመሲህ፣
ሰይጣን እባብ ሆኖ አይመጣም ከእንግዲህ፡፡
ስንፍናችን ታውቆ ለዘር ማደራችን፣
ሰይጣን ተደላድሎ ገባ መሃላችን፡፡
ሁሉ ፍጡር ሆኖ አምላክ የቀረፀው፣
ነገድ ጎሳ ከፍለህ ምነው ተጣላህ ሰው፡፡
“የእገሌ ! የእገሌ ! “ ሲባባሉ ሰምቶ፣
ሰውን ተከትለው ሲከፋፈሉ አይቶ፣
ሐዋርያ የሚሆን የጌታ ክርስቶስ፣
ይህን ተናገረ እንዲህ አለ ጳውሎስ፡፡
“የ አጵሎስ ነኝ ትላለህ አጵሎስ ምን አረገ፣
የጳውሎስ ነኝ ትላለህ ጳውሎስ ምን አረገ፣
ሰው ቢወጣ ቢወርድ ልቡ እንደፈለገ፣
እግዚአብሔር አይደል ወይ ተክሎ ያሳደገ? “
የተወለድክበት ስፍራው ቢነገርህ፣
የሰው ልጅ መሞቻህ አይደል እንዳሳብህ፡፡
ለመቀራረቡ አብሮ ለመብላቱ፣
“ ሰሜን ደቡብ” መባል ባልከፋ ሰርአቱ፡፡
“ምስራቅ ምዕራብ” ብሎ ለጦር መደራደር፣
ያ ነው ግብዝነት መንገድ ስቶ ማደር፡፡
እንግዳ እየሆነ ሚስጥር አይክበድህ፣
ሐቁን ስማ ፍጥረት እውነት ይኸውልህ፣
በአንተ “ሰሜን” መሆን በአንተ ”ደቡብነት”፣
በአንተ “ምስራቅ” መሆን በአንተ “ምዕራብነት”፣
ምን ይገኛል ብለህ ነገድ ከፋፈልህ፣
የስድስተኛ ቀን የእግዚአብሔር ፍጡር ነህ፡፡
እራስክን ከፍ አታድርግ ከማንም አትበልጥም፣
እራስክን ከፍ አታድርግ ከማንም አታንስም፣
አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም፡፡
ከ አዳም የተለየ የዘር ግንድ የለህም፡፡
ሰው አንተን ባይመስል ይዘት ቅርፅ አቋም፣
አይን ጥርስ አፍንጫ ጠጉርና ቀለም፣
የጥቁር የነጩ የ ቀይ የጠይሙ፣
እንደ መልኩ አይደለም አንድ አይነት ነው ደሙ፡፡
ወዶ ቀይ አልሆነም ፈልጎ አልጠቆረም፣
ይኸን መርጦ አመጣው እግዚአብሔር ወደ ዓለም፡፡
አንተ አዘኸው አይደል የሰው ጠይምነት፣
እግዚአብሔር ፈቅዶ ነው የመልክን ልዩነት፡፡
ከየት እንደመጣህ ማስተዋል አትርሳ፣
ምነው ዘር ከመሃል ትቆጥራለህሳ?
ከሰሜን አይደለም ትውልድ አመጣጥህ፣
ከደቡብ አይደለም የዘር መሠረትህ፣
ከምስራቅ አይደለም ጎሳና ነገድህ፣
ከምዕራብ አይደለም የሰው ልጅ እርስትህ፣
መነሻ መፍለቂያ የሕይወት ጅምርህ፣
ካፈር ከተሰራው ከአዳም ነው ግኝትህ፡፡
ሰው ክቡር ነህና ማስተዋል ይብዛልህ፣
የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡


ያቺን ቀን በጸፍ ጸፍ
/ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ/
በአብረሃም ሰሎሞን

ከአዳም ነው ግኝትህ

“እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል፡፡” ኢዮ. 33 ፡14 ፡፡



“እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል፡፡” ኢዮ. 33 ፡14 ፡፡

ክርስትና ጥላቻን አይሸከምም

ክርስትና የተመሠረተው በፍቅር ላይ ነው፡፡ ያውም ሊተረጎም በማይችል ፍቅር ላይ ፡፡ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሠረተው ልዩ ፍቅር ላይ፡፡ የክርስትና መመሪያው “ጠላትህን ውደድ” ነው፡፡ ለዚያውም ክርስቲያን ከዲያብሎስ በቀር ጠላት የለውም፡፡ ግን አንተ ባትጣላውም እርሱ የሚጠላህን፣ አንተ ክፉ ባታደርግበትም እርሱ ክፉ የሚያደርግብህን ውደድ ሲል ነው፡፡

በክርስቲያኖች መካከል ልዩነቶች ባይኖሩ ይመረጣል፡፡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው መኖር ቢችሉ ጠላታቸው ዲያብሎስ ያፍራል፣አባታቸው እግዚአብሔር ይደሰታል፡፡ እነርሱም መለያየት ከሚያስከትለው ፈተና ይድናሉ፡፡ ይሁን እንጂ በክርስቲያኖች መካከል መሠረታዊ ያልሆኑና የሆኑ ልዩነቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ መሠረታዊ ልዩነቶች የምንላቸው በሃይማኖት የተነሳ የሚከሰቱ ልዩነቶችን ነው፡፡ እነዚህ ልዩነቶች ዲያብሎስ በሰዎች እያደረ በሚዘረው እንክርዳድ ምክንያት ሚከሰቱ ናቸው፡፡ አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት ከሚለው የሐዋርያው ትምህርት የሚወጣ /ኤፌ 4 ፡ 5/፡ እውነትን በመቀበልና ባለመቀበል መካከል የሚደረግ ተጋድሎን የሚያስከትል በመሆኑ ከጥንት ጀምሮ የዚህ ልዩነት ምንጩም፣ አመንጭዎችም ሲወገዙ ኖረዋል፡ ይኖራሉም፡፡

ይህም ቢሆን የተለየው ወገን እንዲመለስ፣ እንዲያምን ይደረጋል፣ ካላመነ ካልተመለሰም ተወግዞ ይለያል እንጂ ይውደም ፣ይሙት፣ ይጥፋ ተብሎ ምድራዊ ቅጣት አይታዘዝበትም፡፡የጠላትነት ስሜት ተፈጥሮ /እንዲፈጠር ሆኖ/ ዓይንህን አልየው ድምፅህን አልስማው አይባልም፡፡ እንኳን በሃይማኖት የሚመለሱ ወገኖቹን ይቅርና ሌሎቹንም የሰው ዘሮች ቢሆን ፍቅር ከማሳየት ውጪ የማጥፋትና የማስወገድ መርህ ለክርስቲያን ሊኖረው አይገባም፡፡ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ከሙስሊም ወገኖቻቸው ጋር በተዐቅቦ ተከባብረውና ተፋቅረው የኖሩት በዚህ መሠረታዊ ትምህርት የተነሣ ነው፡፡ የገዛ ወገኖቻቸው ያሳደዷቸውን የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ቦታ ሰጥተው፣ሕይወታቸውን ታድገው፣ለጠላቶቻቸው አሳልፈው ሳይሰጡ የተንከባከቧቸው በዚህ የተነሣ ነበር፡፡

በክርስቲያኖች መካከል መሠረታዊ ያልሆነ ልዩነት ሊኖርም ይችላል፡፡ በዘር፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካዊ አመለካከት፣ በሥልጣን ክፍፍል፣ በሀብት ክፍፍል፣ በዜግነት፣ በመልክና በቁመና፣በዕውቀት፣ ወዘተ… መለያየቶች ቢኖሩም እንኳን ክርስቲያናዊ እምነትና ሕይወት አቻችሎ፣ አስማምቶና አዋህዶ ያለበለዚያም ልዩነቶቹን ኅብረ ውበት አድርጎ ቆጥሮ ይጓዛል እንጂ መሠረታዊውን የፍቅር ኑሮ አናግተው ለጥላቻና ለመለያት አያደርጉም፡፡ ክርስትና የተማረውን /ምሁር የሆነውን/ ጳውሎስ ከዓሣ አጥማጅ ጴጥሮስጋር፣ ቀራጩ ማቴዎስን ከሰዓሊው ሉቃስ ጋር፣ ንጉሡ ካሌብን፣ ከገበሬው ዜና ማርቆስ ጋር፣ሮማዊውን ዲዮናስዮስ ከዕብራዊው ቶማስ ጋር፣ግባጻዊውን አትናቴዎስ ከሶርያዊው ከኤፍሬም ጋር፣ ያስተሳሰረች ሠንሠለት ናት፡፡ የዘር ልዩነቶች የክርስትና ኑሮ ውስጥ ከልዩነት አይቆጠሩም፡፡ ስንዴ ለመገበሪያ የሚውለው የት ተዘርቶ በቀለ በሚል ሳይሆን ስንዴው ራሱ ንጹሕ ነው ወይ? በሚለው መመዘኛ ነውና፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ የሚከበሩትን ያህል በግብጽ ይከበራሉ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተወለደበት ከልዳ በበለጠ በኢትዮጵያ ይከበራል፣ፍሬምናጦስን በሀገሩ በግሪክ የሚያስታውሰው ባይኖርም ኢትዮጵያውያን ግን ከሣቴ ብርሃን እያሉ ያከብሩታል፡፡

ሰዱቃውያን ፈሪሳውያን ጳውሎስ የአመለካከት ልዩነታቸው ወደ ክርስትና እንዳይመጡ አላደረጋቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እርስ በርስ ከማይዋደዱት ከዛግዌ ሥርወ መንግሥት እና ከሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት መካከል ቅዱሳንን ሰይማ ታከብራለች፡፡ ቅዱስ ላሊበላን ቅዱስ ቴዎድሮስን /ወልደ ንጉሥ ዳዊት/ መጥቀሱ ይበቃል፡፡

ፖለቲካዊ አመለካከቶች የርዕዮተ ዓለም ልዩነቶች እንጂ ክርስቲያናዊ ልዩነቶች እና የጥላቻ መንሥኤዎች ተደርገው መወሰድ የለባቸውም፡፡ሶሻሊስቱም፣ ሶሻል ዲሞክራቱም፣ ሪፖብሊካኑም፣ አብዮታዊ ዲሞክራቱም፣ ሌላውም ሌላውም ያላቸውን የአመለካከት ልዩነት ልዩነት አቻችለው በአንዲት ቤተ ክርስቲያን መኖር፣ ማስቀደስ መቁረብ ይችላሉ፡፡ ልዩነታቸው መሠረታዊ አይደለምና ዘርን፣ አመለካከትን፣ ሥልጣንን ወዘተ… መሠረት አድርገው የሚነሱ የጥላቻ ስሜቶችን ለማስተናገድ ክርስተና ቦታ የለውም፡፡ ከባሕሪው ጋርም አይሄድም፡፡ ከቁ ስጥንጥንያ ቤተ መንግሥት የወጣው አርሳንዮስ ከግብጽ ከመጣው መቃርስ ጋር በአንድ ገዳም ኖሯል፡፡ ፍቅር ስላሸነፈ፡፡ ክርስትና እነዚህን ልዩነቶች ድል ነሥቶ የበላይ ካልሆነ የንን ህይወት ክርስትና ነው ማለት ያዳግታል፡፡ አንዱ መለያው ይህ ነውና፡፡ ይህ ወንድሜ አመለካከቱ እንዲሁ ነው፡ እኔ አልቀበለውም ከማለት ባለፈ በዚህ አመለካከቱ የተነሣ አልወደውም፣ እርቀዋለሁ፣ ይጥፋ፣ይሙት በቃ፣ ይወገድ፣ ይውደም የሚለው ዛቻ የተሞላበት አካሄድ ፈጽሞ ክርስቲያናዊ አይሆንም፡፡ ይኸኛው ዘር ይጥፋ፣ ይኸኛው ዘር ይወገድ፣ያኛውን ዘር አትቅረቡ፣ ሌላውን ወገን ውደዱ የሚለው መሥመር ሰይጣናዊ እንጂ ክርስቶሳዊ አይደለም እርሱማ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ነው ያለው፡፡

በመሆኑም ከክርስቲያናዊ የፍቅር ሕይወት ጋር የሚቃረነው የጥላቻ ስሜት በልቦናችን ድሩን እንዳያደራ፣ ፍሬዎቹን መለያትንና መገዳደልንም /መጠፋፋትን/ በመንፈሳዊው የፍቅርና የመቻቻል ሽቱ እናጥፋው፡፡



ወስብሐት ለእግዚአብሔር

እናስተዋውቃችሁ

ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

Read more...

መስቀል

ergbe

“…እቀጣሃለሁ…”
ኤር. 30- 11 በደ/ን ደረጀ ጅማ

በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ብዙ ነገሮች የነገረንና ያስተማረን ልዑል እግዚአብሔር አሁን ደግሞ ብዙዎቻችን ስለምንፈራው ነገር ግን ስለሚጠቅመን ቅጣት ይነግረናል፡፡ የሚሸልም አምላክ እንደ ሆነ የተረዳነውን ያህል የሚቀጣ ንጉሥ መሆኑንም እንድናውቅ ስለፈለገ የመቅጣት ሥልጣኑን በሚገልጥ ቃል “እቀጣሃለሁ”አለን::

እግዚአብሔር ለምን ይቀጣናል?

1.ኃጢአት ከሠራን፡-በባሕሪው ቅዱስ የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር ከኃጢአትና ከርኩሰት የተለየ ሕይወት እንዲኖረንና በዚህ ዓይነቱ ሕይወት እንድንኖር ይፈልጋል፡፡ጥንቱንም የጠራን ለቅድስና ነውና፡፡ ወደ ክርስትና ሕይወት የተጠራንበትን ይህን የመሰለ ዓላማና ሕይወት ዘንግተን ኃጢአትን እንደ እሕል ስንበላ እግዚአብሔር ዝም አይልም፡፡ የተዘፈቅንበትን ኃጢአት ጥለን እንድንወጣና ንስሀ እንድንገባ ዘወትር የሚያያሳስበን እግዚአብሔር በሠራነው ኃጢአት ይቀጠናል፡፡ “ሰው ስለ ኃጢአቱ የሚያጉረመርም ስለምንድን ነው?” ሰቆቃው ኤርሚያስ 3- 9 ፡፡የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ስናነብ እግዚአብሔር የቀጣንና የሚቀጣን በኃጢአታችን የተነሣ መሆኑን አንዘንጋ፡፡::

2.ልጆቹ ስለሆን፡-በሥጋ ሁላችንም የተለያዩ ምድራዊ አባቶች አሉን፡፡ በአግራሞት እንድንሞላ የሚያደርገን እውነታ ግን ከተለያዩ ምድራዊ አባቶች የተወለድን እኛ የአንዱ እግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ነው፡፡ ከየትም እንመጣ አባት ብሎ ሆኖ በልጅነት ክብር ተቀብሎናል፡፡ “እኔም እቀበላችኋለሁ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ” እንዳለ፡፡ 2ኛቆሮ. 6-18 ፡፡ የእርሱ ልጆች ሆነን እርሱ አታድርጉ ያለንን ካደረግን ወይም ከፈጸምን ግን ያለ ቅጣት አይተወንም፡፡ በዚህ ጊዜ የምንቀበለው ቅጣት የእግዚአብሔር የጭካኔ በትር ሳይሆን ዲቃላ ያለመሆናችንን ወይም የእግዚአብሔር ልጆች የመሆናችን ማረጋገጫ ነው፡፡አባት የሚቀጣው ልጅን አይደል? ልጄ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቃልል በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡፡ “”…..እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርጋችኋልና አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና፡፡ ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደለችሁም፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን አንፈራቸውም ነበር፡፡ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይቀወት ልንኖር በተገባን? ”ዕብ. 12፡ 6-9፡፡


3. ስለሚወደን፡- ሁላችንም የማንክደውና ባስታወስነው ቁጥር ሐሴት የምናደርግበት አንድ ሐቅ አለ፡፡ያም እግዚአብሔር ለኛ ያለው ንጹህ ፍቅር ነው፡፤ በነቢዩ ሚልክያስ ላይ አድሮ “ወድጃችኋለሁ” ያለውም በዚህ ነው ፡፡ ሚል. 1፡ 2፡፡ ምንም የሌለን ስንሆን እንዲሁ ነው የወደደን፡፡ በመሬት ላይ ከሚኖሩ ፍጥረታት አፍ ያልተገኘልን ወረተኞች እርሱ ግን እስከ መጨረሻው ወደደን፡፡ ሳያበላልጥ እኩል፣ አንዳች ሳይቀበል በነጻና እስከ መጨረሻው የወደደን አምላክ ባጠፋን ጊዜ ቢቀጣን አንደነቅ፡፡ በሥጋ የወለዷቸው ልጆች ባጠፉ ጊዜ ስለ ማይወዷቸው ብቻ በዝምታና በምን አደከመኝ እያለፉ ልጆቻቸውን ለበለጠ ጉዳት የዳረጉ አባቶች አሉ፡፡ አባታችን እግዚአብሔር ግን እንደነዚህ አባቶች አይደለም፡፡ ስለ ወደደን የሚጠብቀን ስለ ወደደንም ይቀጣናል፡፡ ከፍቅሩ የተነሣ የሚምረን ጌታ ከፍቅሩ የተነሣ ይገርፈናል፡፡ እሱ እኛን የሚቀጣን ልጆቹ ብቻ ስለሆን ሳይሆን ከየትኛውም ፍጥረት በላይ ስለሚወደን ነው፡፡ ጠቢቡ ሰለሞንም “ልጄ ሆይ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር፡፡ እግዚአብሔር የወደደውን የገሥጻልና አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ” ያለው ለዚህ ነው፡፡ ምሳ. 3፡ 11- 12፡፡


4. ለጥቅማችን፡- እያንዳንዳችን ለራሳችን የሚበጀንን የምናውቅና ከሚጎዳንም የመራቅ እውቀት እንዳለን በማሰብ እንኩራራ ይሆናል፡፡ የድርሻችንን ለመወጣት መጣራችን የሚያስመሰግነን ቢሆንም የኛ ለእኛ ማሰብ እግዚአብሔር ለኛ ከሚያስበው ጋር ሲነጻጸር ግን ትምክህታችንን ውኃ ይበላዋል፡፤ የኛ ድንግ ዝግና ከፊል ሲሆን የእግዚአብሔር ግን የጠራና ምሉዕ ነው፡፡ እኛ የሚጠቅመን መስሎን የሚጎዳንን ለመያዝ ስንሮጥ እሱ ግን ለሥጋችን ጉዳት በመሰለ ነገር የሚጠቅመንን ነገር ይሰጠናል፡፡ “ለእናንተ የማስባትን ሃሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም፡፡” ኤር. 29፡ 11፡፡ ነገሮችን ሁሉ ለእኛ ጥቅም የሚያደርግ እግዚአብሔር ሲቀጣንም ሊጠቅመን ፈልጎ ነው፡፡ የእርሱን ቅጣት ከጭካኔና ከብቀላ አንፃር የምንመነዝር ሰዎች በቅጣት ቅርጫቶች ውስት የተከማቹትን ጠቃሚ የዌን ፍሬዎች ያልተመለከትን ነን፡፡ ሲነጥቀን ሊሰጠን ሲሰብረንም ሊጠግነን ነው፡፡ ሲያስለቅሰን ሊያስቀን ሲጥለንም ሊያነሣን ነው፡፡ ሲያቆስለን ሊፈውሰን ሲያዋርደንም ሊያከብረን ነውና አሠራሩን
በማስተዋል እንመልከት፡፡ ይህንን በሕይወቱ የቀመሰው ቅዱስ ጳዉሎስ እንዲህ ብሏል፡፡ “እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለገዛ ጥቅማችን ይቀጣናል፡፡” ዕብ. 12፤ 10፡፡ ዘወትር በአንድና በሌላ መንገድ መናገር የሚወድ እግዚአብሔር ሲቀጣም በተለያየ መንገድ ነው፡፡ የትናውንም ጎዳና ተጠቅሞ ወደ እኛ ሲቀርብ ግር አይበለን ፡፡አንቆጣ ፡፡ አናማርር፡፡ በተለያየ መልክ ቢላክም የእግዚአብሔር ቅጣት የእግዚአብሔር ነው፡፡ በቅጣቱ ለመመለስ፣ ለመማር፣ አስተዋይ ለመሆን መለማመድ ይኖርብናል፡፡



እግዚአብሔር ሲቀጣን ምን እናድርግ?


1.አናጉረምርም፡- በእርግጥ እየተገረፍን መሳቅ እየተቆነጠጥንም መፈንደቅ ስላልለመድን የእግዚአብሔርን ቅጣት ያለ ማጉረምረም የተቀበልንት ቀን አይኖር ይሆናል፡፡ ክርስትና ግን የማይመስለው የሚመስልበት ሊሆን የማይችለውም ሲሆን የሚታይበት ሕይወት ነው፡፡ ስለዚህ የተቀበልነው ቅጣት ምንም ከእሬት ቢመር በውስጡ ያለውን ጣፋጭ የእግዚአብሔር ዓላማ በማሰብና ቅጣቱን በዝምታ እንደሚቀበል አስተዋይ ብላቴና በመሆን በቅጣታችን ጊዜ ከማጉረምረም እንቆጠብ፡፡ ማጉረምረም ከማያምኑ ሰዎች /አሕዛብ/ መንደር የማይጠፋ ክፉ ልምድ ነው፡፡ “”አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ” የተባለላቸውም ለዚህ ነው፡፡ መዘ. 2፡1 ፡፡ የአምልኮት መልክ ኖሯቸው ኀይሉን የካዱ አይሁድም በዚህ ግብር የታወቁ ነበሩ፡፡ እኛ ግን ኢ-አማንያን ሳሆን አማንያን ነን፡፤ የአምልኮት መልክ ኖሯቸው ኄሉን እንደካዱት ኤደለንም፡፡ ኀይሉን አምነን የአምልኮት ሥርዓት የምንፈጽም ነን እንጂ፡፡ስለሆነም እግዚአብሔር ሲቀጣን አናጉረምርም፡፡ ማጉረምረማችንን እርሱ ያውቃልና፡፡ በዚህ ድርጊታችንም ስለሚደነቅ “ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጉረመርም ስለ ምንድን ነው?” ይላል፡፡ ሰ. ኤር. 3፡ 39 ፡፡ አምላካችን ይህንን ያለው በኃጢአታችን የተነሳ የመጣብንን ቅጣት በማጉረምረም መቀበላችንን ተመልክቶ ብቻ ሳይሆን እየተቀበልን ያለው ቅጣት ከሠራነው ኃጢአትና መተላለፍ ጋር ሲነነጻጸር እጅግ በጣም አናሳ ስለሆነ ነው፡፡ ከበደላችን አሳንሶ የሚከፍለን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ “እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ” ተብሎ መጻፉን ልብ እንበል፡፡ ኢዮ. 11ሚ. 6፡፡በደረሰብን ቅጣት የምናጉረመርም ሁሉ ወይ መቀጣት የለብኝም አለበለዚያ የእግዚአብሔር ቅጣት በዝቶብናል የምንል ነን፡፡ ይኼ ደግሞ ሌላ ሰቆቃ እንደሚወልድ አንጠራጠር፡፡ ይህ እንደይደርስብንና ባለማጉረምረማቸው የተነሣ የተሸለሙትን የእግዚአብሔር ሰዎች እድል እኛም እንድናገኝ ስንቀጣ አናጉረምርም፡፡

2.እንታገሥ፡- በየትናውም የሰው ልጆች የህይወት ውጣ ወረድ ውስጥ ትዕግሥት ያበረከተላቸውና አስተዋጽኦ ያስገኘላቸው ዋጋ ታላቅ ነው፡፡ በትዕግሥት የጸለየ የለመነውን ሲቀበል በጽናት የተጋደለም የድልን አክሊል ይቀዳጃል፡፡ ወደ ህይወታችን የመጣውን የእግዚአብሔር ቅጣት በትዕግሥት ማስተናገድ ከቅጣቱ ጀርባ የተቀመጠውን ሽልማት ለመቀበል ያስችለናል፡፡ ንጉሥ ዳዊት የተቀበለውን አስጨናቂ ቅጣት በትዕግሥት በመሸከሙ በረከትና እረፍት የመላበትን ሕይወት ለመምራት ችሏል፡፡ ዛሬም በቅጣት ወኅኒ ውስጥ ወድቀን በቅጣት ሰንሰለት የታሰርን ሁሉ በትዕግሥት ጨለማ አብቅቶ የእረፍትና የእፎይታ ፀሐይ የወጣልናል፡፡ መራራውም የቅጣት ጽዋ በጣፋጭ ይሕይወት መጠጥ ይሞላል፡፡ ስለዚህ “ለመቅጣት ታገሡ” ዕብ. 12፡ 7፡፡ በሚለው አምላካዊ ቃል እየተደገፍን ቅጣታችንን በትዕግሥት ለመሸከምና ለመፈጸም እንበርታ፡፡

3.ደስ ይበለን፡- እግዚአብሔር የደስታ ምንጭ ነው የሚባለው ከደስታ ደመና ላይ የደስታ ዝናም ስለሚዘንብልን ብቻ አይደለም፡፡ እርሱ ሁሉን ቻይ ከመሆኑ የተነሣ በቅጣት ድንጋይ ከተሞላ የሕይወት ውጣ ውረድ ላይ የደስታ ምንጭ ማፍለቅ ይችላል፡፡ ምክንያቱም በእርሱ ፈቃድ ወደ ሰው ልጆች ሕይወት የሚገቡ ቅጣቶች ሁሉ ለጊዜው ቢያሳዝኑንም በመጨረሻ ግን ኀዘን የሌለበትን ደስታ ፈጥረውልን ያልፋሉና፡፡ ሕመምና ማጣት በበዛባት የቅጣት መንገድ ላይ ተቁሞ አንዴት ደስታ ይታሰባል ይባል ይሆናል፡፡ መልሱ እግዚአብሔር ደስታችንን ናፋቂ ከመሆኑ የተነሣ የቆምንበት የቅጣት ጎዳና በደስታ ወደ ተከበበ የሕይወት ስፍራ እንዲያደርሰን ማድረግ ይችላል ነው፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጠ የደስታ መሬት ላይ የቆመ ክርስቲያን ሁሉ ሰላምና ጽድቅን እንደሚያፈራ እንወቅ፡፡ “ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፡፡ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል” እንደተባለ፡፡ ዕብ. 12፡ 11፡፡ በደስታ ከምንቀበለው ቅጣት ውስጥ የሚገኘውን ሰላምና ጽድቅ ለመቀበል እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ልጆቹ ስለሆንና ስለሚወደን እንዲሁም ኃጢአት እንድንሠራና በዚያም ጸንተን እንድንኖር ስለማይፈልግ ስለእኛ ጥቅም ሲል ይቀጣናል፡፡ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ /ፈራጅ/ ነውና በነገር ሁሉ ትክክለኛ ፍርድ ስለሚሰጥ ቅጣቱ ትክክለኛ መሆኑን በመገንዘብ ያለማጉረምረም፣በትዕግሥት ዕሴት እያደረግን /እየተሰማን/ ፍርዱን ለመቀበል ህይወታችንን ማለማመድ ይገባናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሕይወት እንዲኖረን ሁሉን የሚያስችል ልዑል አምላካችን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር



በአንበሳና ነብር የምትጠበቀው የአበልቲ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተመረቀች

በጅማ ሀገረ ስብከት ሰኮሮ ወረዳ በአንበሳና በነብር የምትጠበቀው የአበልቲ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና የአ ቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡ በገቤ ወንዝ ድልድያ አጠገብ በረሐ ውስጥ የምትገኘው አበልቲ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን albelti የተተከለችው በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሲሆን በኋለም በ1944 ዓ. ም በቀ ዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴና በጅማው ገዢ በራስ መስፍን ስለሺ አማካኝነት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል፡፡በዘመነ ደርግ ተመልካችና እንክብካቤ በማጣቱ የሕንፃው ግማሽ አካል ፈርሶ ቆይቷል፡፡ከዚያ በኋላ በግልገል ጊቤ ፕሮጀክት የነበረ የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ካንኒ ሠራተኞች ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን ለመሥራት ባደረጉት ጥረት ሐምሌ 17 ቀን 1995 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ፡፡ከሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ በተጨማሪበአበልቲ የመነኮሳት መኖሪያ ቤትና መንበረ ጵጵስና ተሠርቷል፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ለአራቱ አህጉረ ስብከቶች ጋምቤላ፣ኤሊባቡር፣ከፋሽካ ቤንች ማጂና፣ ጅማ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ሌሎችም ብፁአን አባቶች ለሐዋርያዊ አገልግሎት ሲፋጠኑ በዚሁ ገዳም አርፈው ለአካባቢው ሕዝብ ቡራኬያቸውን ሰጥተውና አስተምረው እንዲሄዱ ታስቦ የተሠራ መሆኑን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ገልጸዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን በበአሉ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት “ለሰባት ዓመታት የጅማ ከፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበርኩ፡፡ ቤተክርስቲያን አሠርቻለሁ፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ለማሠራት ብዬ ጫካ አላደርኩም፡፡ ብፁዕ አቡነ አስጢፋኖስ ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማሠራት ጫካ ከአናብስት እና ከአናብርት ጋር፣ ዝንብና የወባ ትንኝ በበዛበት፣ የሚጠጣ ንፁህ ውኃ፣ የሚበላ የላመ ምግብ በሌለበት በረሐውን ታግሰው ምእ መናንን አስተባብረው የአበልቲ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያንን ማሠራታቸው የሚደነቅ ነው፡፡ እኮራባቸዋለሁ፡፡ ምእ መናንም የብፁዕነታቸውን ሥራ ተንከባክበው ገዳሙ ራሱን እስኪችል በልማት፣ በጎጆ ኢንዱስትሪዎች ማጠናከር አለባቸው” ብለዋል፡፡

አበልቲ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም በታላቁ የጊቤ ወንዝ አጠገብ የምትገኝ ሲሆን በአናብስትና በአናብርት የምትጠበቅ ናት፡፡ በዋዜማው እንኳ አራት አናብርት በቤተ ልሔሙ ዙሪያ ታይተዋል፡፡ ቦታው ብዙ ቅዱሳን ያሉበት ነው፡፡ የፈለቀ ጠበል ያለበት በመሆኑ በርካታ ምእመናን ከቅርብም ከሩቅም በመምጣት እየተጠመቁ ከተለያዩ ደዌ እየተፈወሱ መሆናቸውን የጅማ ሀገረ ስበከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ መዘምራን ብርሃኑ ጌጤ ገልጸውልናል፡፡

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኗን ለማስፈጸም በዛው በአበልቲ በአቢይ ጾም ሱባኤ በመያዝ ከሠራተኞች ጋር አብረው በመሥራት እያበረታቱ ለፍፃሜ አብቅተውታል፡፡ በርካታ ምእመናን ከአዲስ አበባ እና ከጅማ እንዲሁም የሳሊኒ ካምኒ ሠራተኞች ከአካባቢው ከተሞች በመምጣት ለሕንፃው ሥራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን፣ አሸዋ ሲሚንቶ፣ ቆርቆሮ፣ ብረት፣ ወዘተ… አቅርበዋል፡፡ በጉልበት፣ በገንዘብ፣ረድተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ የአጥቢያው ሕዝብም በጉልበታቸው ውኃ በመቅዳት የሚያስፈልገውን ሁሉ በመተባበር የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ ለፍፃሜ እንዲደርስ አድርገዋል፡፡ በሀገርም በውጭም ያሉ በጎ አድራጊ ምእመናን ንዋየ ቅድሳቱን፣ ምንጣፉን፣ ቅድሳት ሥዕላተሩን በመግዛትና በማምጣት አሟልቷል፡፡

በአበልቲ ቀበሌ ዙሪያ የሚገኙ ምእመናን ቁጥር ከሃያ የማይበልጡ ናቸው፡፡ ነዋሪዎቹ በዋዜማው በዓሉን ለማክበር ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጡት ምእመናን ”እንግዳ መቀበል ያለብን እኛ ነን “ ብለው በሀገራቸው ባህል በሬ አርደው ሕዝቡን ጋብዘዋል፡፡

ግንቦት 20 ቀን 1998 ዓ. ም. የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ በተመረቀበት ዕለት ብፁዕነታቸው በዓሉን ለማክበር ለመጣው ሕዝበ ክርስቲያን ለብቻ ለአካባቢው ሙስሊም ኅብረተሰብ ለብቻ መስተንግዶ አድርገዋል፡፡በበዓሉም ብፁእ አቡነ ጢሞቲዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀዉስጦስ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የአበልቲ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ቤተ ክርስቲያንን ለማሳደግ በርካታ ዕቅድ እንደተያዘና ተግባራዊ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ለአካባቢው ሰው እንዲያገለግል የእህል ወፍጮ ለማስተከል በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የአካባቢው ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በኦሮምኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተምረው ዲያቆን፣ ቄስ ሆነው ነገ ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ዘመናዊና መንፈሳዊ ትምህርት ያካተተ ት/ቤት ለመክፈት በዕቅድ ተይዞ ለተግባራዊነቱ የሚደረገው ጥረት ቀጥሏል፡፡ የአካባቢው ሕዝብ ለቤተ ክርስቲያን በሰጠው ሦስት ሔክታር መሬት ላይ የተለያዩ ልማቶችን ለማከናወን ታቅዷል፡፡ ምእመናን አሁን እንዳበረከቱት አስተዋጽኦ ወደ ፊትም ከጎናቸው በመሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ገዳሙን በገንዘብ ለመርዳትና ለማጠናከር የምትፈልጉ አድራሻው አበልቲ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስተ ኪደነ ምህረትና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅማ ዐቢይ ቅርንጫፍ የባንክ ቁጥር 30559 ፡፡



በእስልምና ስም በሚንቀሳቀሱ አክራሪ ኃይሎች ተገደው እንዲሰልሙ የተደረጉ ክርስቲያኖች ወደ ሃይማኖታቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ገለጹ

በኢሊባቡር እና በጅማ አህጉረ ስብከት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በእስልምና ስም በሚንቀሳቀሱ አክራሪ ኃይሎች ተገደው እንዲሰልሙ የተደረጉ ክርስቲያኖች ወደ ሃይማኖታቸው መመለስ እንደ ሚፈልጉ ገለጹ፡፡
በጅማ ዞን በጎማ እና በጉ ማይ ወረዳዎች የተቃጠለው የጨጎ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባዔ አባል አቶ ጌታቸው ጎንደር እና የሰበካው ገንዘብ ያዥ አቶ ጥላሁን በቀለ ተገደው ሰልመዋል፡፡ በዚህ ወረዳ ሕፃናትን ሳይጨምር ከ156 /ከአንድ መቶ ሃምሳ ስድስት/ በላይ ክርስቲያኖች የእስልምናን እምነት ያለፈቃዳቸው እንዲቀበሉ ተደርገዋል፡፡በያጪ ኡረች ቀበሌ አቶ ሀሩ ያደታ፣ አቶ ዝናቡ ከበደ፣ ወ/ሮ አረጋሽ ገለታ፣አቶ አያና ተሰማ፣አቶ ዝናቡ ከበደ /አብዱል ቃድር/፣ አቶ ተሰማ /ጀማል/፣ አቶ ዘመኑ መኩሪያ /መሐመድ አሚን/እንደገለጸት “ሰላም ሆኖ ወደ እምነቴ እስክመለስ ድረስ እግዚአብሔር ያውቃል ብዬ ሰለምኩ” ብለዋል፡፡

በጉማይ ወረዳ በቦሬ ጉዳ ቀበሌ እንደዚሁ 46 ሰዎች ተገደው የሰለሙ ሲሆን የ56 /ሐምሳ ስድስት/ ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት አቶ ታከለ ገብረ እግዚአብሔር እንደለጹት ንብረታችሁን ከምናቃጥል እናንተንም ከምናጠፋ ስለሙ፣ ከሰለማችሁ አትነኩም” አሉን፡፡ እኔም ሰለምኩ በድሩ አሉኝ፤ያሉት አቶ ታከለ፤ መስጊድ ይርቀኛል አልሄድም ብላቸው አንድ እስላም አሰጋጅ መድበውልኝ እርሱ ቤቴ ድረስ እየመጣ ያሰግደኛል፤ ባለቤቴ እና ልጆቼም ሰልመዋል ብለዋል፡፡ አቶ ታከለ አያይዘውም “ወደ ሃይማኖቴ እመለሳለሁ እንጂ በዚሁ የመቅረት ሐሳቡም ፈጽሞ የለኝም የሚያስተምረን፤ የሚባርከን አባት ቢሰጠን ሃይማኖታችንን መተው አንፈልግም ሲሉ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና የሥራ ኃላፊዎች አስረድተዋል፡፡፡፡



የተሰቀለውን ክርስቶስን እንዳታስተውሉ ማን አዚም አደረገባችሁ?

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማምና መከራ ከመወለዱ በፊት አንስቶ እንዳልተለየው መጽሐፍት ያስረዳል፡፡ ከእነዚህ ሕማማትና መከራ እጅግ አብዝቶ የተቀበለው ቤዛነት በሚፈጽምበት በመጨረሻ ወቅት ነበር ፡፡
አዳም የፈጠረውንና የሚወደውን አምላኩን በመበደሉና ትዕዛዙን በመጣሱ ከእግዚአብሔር ተጣልቶና ተለይቶ ይኖር ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ሕማም መከራ ውድቀትና ውርደት ደረሰበት፡፡ በሰውና በእግዚአብሄር ትልቅ የጥል ግድግዳ ተፈጠረ፡፡ እግዚአብሄር አምላክ ርኅሩኅ ስለሆነ የአዳም ስቃይ ስላሳዘነው ሊታረቀው አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፡፡ እርሱም ሁለተኛው አዳም በመባል ክርስቶስ ኃጢአት በሌለበት ሰውነቱ የመጀመሪያው ሰው የአዳምን ኃጢአት ተሸክሞ የእርሱን ሞት ሞቶ በመስቀል ላይ የሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል ከራሱ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ አስታርቆታል፡፡ ይህንንም ነቢየ ልዑል ኢሣያስ በትንቢቱ ከሰባት መቶ ዓመት በፊት እንዲህ ብሎ ገልጾት ነበር፡፡

“በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕማማችንን ተሸክሟል፣ እኛ ግን እንደተመታ በእግዚአብሔር እንደ ተቀሰፈ እንደተቸገረም ቆጠርነው፡፡እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፣ ስለበደላችንም ደቀቀ፣ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበር፣ በእረሱም ቁስል እኛ ተፈወስን… ተጨነቀ ተሰቃየ አፉንም አልከፈተም፣ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፣ በሽላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፡፡ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመቶ ከሕያዋን ምድር እንደተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ከክፉዎች ጋር መቃብሩን አደረጉ…”/ ኢሣ. 53 ከ 6- 12/

ጌታችን ሕማምና ሞቱ በተቃረበ ጊዜ በመጀመሪያ ምስጢረ ቁርባንን የ ጸሎተ ሐሙስ ማታ መስርቷል፡፡ ለዚህም የኦሪትን መስዋዕት ፈጽሞ በምትኩ የሐዲስ ኪዳንን መስዋዕት ሠርቷል፡፡ ኅብስቱንና ወይኑን ለውጦ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ የተሰዋውን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አድርጎ ለሐዋርያት ሰጥቷቸዋል፡፡ /ሉቃ. 22 ቁ19- 20/ ይህንንም የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ ትፈጽመዋለች፡፡ በዚያም ምሽት የዓለምን ኃጢአት ለማስወገድ ለአዳምና ለልጆቹ መራራ የነበረውን የሞት ጽዋ ለመቀበል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተዘጋጀ፡፡ በነፍስም በሥጋም መከራን ተቀበለ፡፡ ጌታችንም አይሁድ ለፍርድ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ሸንጎ አቀረቡት፡፡ መረመሩትም፣ ክፋትም አላገኙበትም፡፡ በመጨረሻ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆነ ጠየቁት፡፡ እርሱም በእርግጥ ክርስቶስ እንደሆነ መለሰላቸው፡፡ ይህንንም እንደ ታላቅ ወንጀል ቆጥረው ሞት ይገባዋል፡፡ ብለው ፈረዱበት፡፡ “በዚያን ጊዜ ገረፉት፣ በፊቱ ተፉበት፣ ጎሰሙት፣ በጥፊም መቱት…” /ማቴ. 26 47- 58/፡፡ ጌታችንንም የሚሰቀልበትን መስቀል አሸከመው ወደ ቀራንዮ ኮረብታ እንዲወጣ አደረጉት፡፡

ከዚያም እጁንና እግሩን በቀኖት /በምስማር/ ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል ሰቀሉት፡፡ ሐሞትና ከርቤን ቀላቅለውም አጠጡት፣ ጎኑንም በጦር ወጉት፡፡ /ማር. 13 ቁ 25፣ ዮሐ. 19- 19/፡፡ በዚህም በሰባቱ አጽርሐ መስቀል እንደ ሆነው ቃሉ “ ተፈጸም” ብሎ ወደ ዚህዓለም የመጣበትን የሰው ልጅን የማዳን ጉዞ በቀራንዮ አደባባይ ፈጸመ፡፡

ክርስቲያኖች እንግዲህ የጌታ ሕማሙን ስናስብ የድኅንነታችን ጸጋ መንጭ የሆነውን የተሰዋውን የባህርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን እናስተውላለን፡፡ ጌታችን በመስቀል ላይ በሥጋው ሞቶ በነፍሱ ደግሞ በታላቅ ግርማ መለኮት በመገለጡ ከአዳም ጀምሮ በዲያብሎስ ግዛትና በሲኦል ግዞት ውስጥ ለነበሩት ነፍሳት ሁሉ ነጻነትን ሰበከላቸው፡፡ “ዛሬ ከእኔ ጋር በነፃነት ትሆናለህ” በማለት ክርስቶስ ለፊያታዊ ዘየማን የሰጠውን ተስፋ በዚያ ጊዜ ፈጸመው፡፡ /ሉቃ. 23 43/

በዕለተ ዓርብ በክርስቶስ ገነት ከተከፈተች በኋላየቅዱሳን ነፍሳት እሰከ ዳግም ምጽአት የሚቆዩበት ስፍራ ከዚያው ከገነት ሲሆን በመጨረሻ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ይገባል፡፡ የኃጥአን ነፍሳት ግን ለጊዜው በሲኦል ቆይተው በመጨረሻው የፍርድ ቀን ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ከተዘጋጀው ገሀነመ እሳት ሁለተኛ ሞት ካለበት የእሳት ባሕር እንዲገቡ ይፈረድባቸዋል፡፡ /ራዕ. 20 14/

በክፉ ሥራቸው ተጸጽተው ንስሀ ገብተው የጌታቸውን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የተቀበለ ሁሉ የሰላምና የደስታ ሕይወት ከገነት ይጠብቃቸዋል፡፡በአመጻቸው ጸንተው ንሥሀ ያልገቡ በሰማይም በምድርም ምህረት አያገኙም፡፡ ምክንያቱም በምድር ከኃጢአታቸው አልተፈቱምና ነው፡፡ ኃጢአታቸው በምድር የተያዘባቸው ከሆነ በሰማይ እንደ ተያዘባቸው ይቀራል፡፡ /ዮሐ. 20 23፣ ማቴ. 18 18፣ ማቴ. 16 19/

ስለዚህ ክርስቲያኖች ወደ ንስሀ ቀርበን ቀዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን ተቀብለን መንግሥቱን እንድንወርስ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማምና መከራ ሁልጊዜ ከህሊናችን እንዳለ የገባዋል፡፡ በዚህም በጌታችን ትንሳኤ ትንሳኤ እንደሚኖረን ከሞት በኋላ ሕይወት እንዲል እንረዳለን፡፡ እንግዲህ ቸርነቱና ምህረቱ የማያልቅበት አምላክ በንሥሀ ሕይወት እንድንመላለስ ለቅዱስ ሥጋው ለክቡር ደሙ እንድነበቃ ምንግሥቱን እንድነውርስ ይርዳን፡፡ አሜን



አንዳንድ ዘማሪያንና መዝሙሮቻቸው ወዴት እየሄዱ ነው?

በተለያዩ ዘማርያን ተዘጋጅተው የሚሠራጩ አንዳንድ መዝሙራት ከዘፈን በተገለበጠ ዜማ ነው ሲሉ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ሐላፊዎችና ምዕመናን ገለጹ፡፡ በወርኃዊና ዓመታዊ ንግሥ በዓላት ላይ ከፍተኛ የድምጽ ማጉያ በመጠቀም የሚደረገው የመዝሙር ካሴት ሽያጭ ስብከተ ወንጌሉንና ሥርዓተ ቅዳሴውን እያስተጓጎለው መሆኑን ተጠቆመ፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባኤና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ፣ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ሐላፊዎች መጋቤ ሐዲስ ሐዋዘ ብርሃን ጫኔና መጋቤ ትፍስት ግርማ አሰፋ እንዲሁም አንዳንድ ምእመናን እንደገለጹት ቤተክርስቲያን የዜማ ሀብታም ብትሆንም ዘማርያኑ ግን ከዘፈን ዜማ በመገልበጥ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በማፋለስ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

በቤተ ክርስቲናችን የዜማ ሊቃውንትና ሰፊ ያሬዳዊ የዜማ ሀብት እያሉን በዘፈን ዜማ መዝሙርን ማዜም የሚያሳዝን መሆኑን የጠቀሱት ሐላፊዎቹ ቤተ ክርስቲያን ለእንዲህ ዓይነቱ ሥርዓት ያጣ አካሄድ አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት እንደሚኖርባት አሳስበዋል፡፡

ባለሁበት ሐላፊነትና እንደ አንድ ምእመን ሆኜ ሳየው መዝሙር አጠቃላይ ሒደቱ ሥርዓቱ መሥመር እየሳተ ነው፡፡ ያለ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሚሔድ ነገር ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ሊያስነቅፉት እንደሚችል መገንዘብ ይገባል በማለት መጋቤ ሐዋዘ ብርሃን ጫኔ ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት ምእመናን መዝሙር የማዳመጥ ፍላጎት ቢኖረንም አንዳንድ መዝሙራት ግን በሚታወቁ የዘፈን ዜማ በመዜማቸው በኅሊናችን ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እየደረሰብን ነው በማለት አማረዋል፡፡ የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ጉዳዩን በቸልታ ማየት እንደሌለባቸውም አሳስበዋል፡፡
በተያያዘም በየ ቤተ ክርስቲያኑ አጥር ጥግ ከፍተኛ የድምጽ ማጉያ በመትከል የመዝሙር ካሴት የግዙኝ ጩኸት የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ሥርዓተ ቅዳሴውን፣ ትምህርቱን፣ ጸሎቱን እያደናቀፈ መገኘቱን መጋቤ ሐዲስ ሐዋዘ ብርሃን ጫኔ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዚህ ዙሪያ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምት ተጠይቀው መልስ የሰጡት ሐላፊው “አንዳንድ መዘምራንን በግል በመቀራረብ ደረጃ አነጋግረናቸዋል፡፡ ድርጊቱ ፈር የለቀቀው መሆኑንም አሳውቀናቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ የሚሰጡት ምላሽ እነርሱ /ዘማሪዎቹ/ በዚህ ድርጊት ወሳኝ ሚና እንደሌላቸው ገልጸውልናል፡፡ ስለዚህ ችግር የተፈጠረው ከአሳታሚዎች በኩል መሆኑን ነው የሚገልጹት፡፡ ያም ሆነ ይህ ለችግሩ መከሰት ሁለቱም ወገኖች የራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡” በማለት መጋቤ ሐዲስ ሐዋዘ ብርሃን ጫኔ አስታውቀዋል፡፡ የመዝሙር ካሴት አሳታሚዎችም ቢሆኑ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን በላይ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እና ምእመናንን የሚያውክ ከሆነ ሊያቆሙ ይገባል፡፡ ለማንኛውም ጉዳዩን ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ትኩረት ሰጥተውበታል፡፡ ወደ ፊት በዚህም ሆነ በዘፈን ዜማዎች በሚዘመሩት መዝሙራት ላይ ውሳኔ ይሰጥበታል በማለት ሐላፊው አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት የሚገኙ ሰባክያነ ወንጌል ጥር 19 ቀን 1998 ዓ.ም. ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ጳጳስ ሰብሳቢነት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ አጠቃላይ ስብሰባ ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ በሊቀውንት ቤተ ክርስቲያን ያልተመረመረና ያልተፈቀዱ ልዩ ልዩ የመዝሙር ኦዲዮ ቪዲዮ ካሴቶች፣መጽሐፍቶች እየተሸጡ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ይህም ከትምህርተ ወንጌል ይልቅ ዓውደ ምህረቱ የሽያጭ መድረክ እየሆነ መምጣቱ የሚያሳስብ መሆኑና ምእመናንም የሚሰጠውን ትምህርተ ወንጌልን ለመስማት መቸገራቸውን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል መምሪያ ሐላፊ የሆኑት መጋቤ ትፍስሕት ግርማ አሰፋ ገልጸዋል፡፡
ጉዳዩ አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ በሀገረ ስብከቱና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ታይቶና ተመርምሮ ሳይፈቀድ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ደንብ የተዘጋጀ” በማለት በአብያተ ክርስቲያናቱ የሚሸጡ የመዝሙር ካሴቶች አግባብነት የላቸውም፡፡ የተፈቀዱትም ቢሆኑ ቃለ እግዚአብሔር በሚሰጥበት ሰዓት ሳይሆን ሽያጩ ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲካሄዱ መወሰኑን መጋቤ ትፍስት ግርማ አሰፋ አስረድተዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከሥራ መደራረብ የተነሣ ጊዜ በማጣታቸው እንጂ የውሳኔ ሐሳቡ ለአብያተ ክርስቲያናቱ ተልኮ ተፈፃሚ እንዲሆን ይደረጋል በማለት መጋቤ ትፍሰት ግርማ አሰፋ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦዲዮቪዥዋል አሳታሚዎች ማኀበር በበኩሉ “ሰንፔር” በሚል ርእስ የተዘጋጀውን መዝሙር አስመልክቶ EA VPAA AA 0324ሐ0005 ጥር 22 ቀን 1998 ዓ. ም. ለአባላቱ በሙሉ በሚል ርእስ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ ደብዳቤው ሎዛ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት ያሳተመው የቪ.ሲ.ዲ. መዝሙር የሙያተኞችን መብት ያልጠበቀ ከእምነቱ ሥርዓት ያፈነገጠ ነው የሚል ቅሬታ እንደቀረበበትና ጉዳዩ እስኪጣራ መዝሙር ምንም ዓይነት የሽያጭና የማከፋፈል ተግባር እንዳይፈጸም ማስታወቁን ይገልጻል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በየወሩ እየታተመ የሚወጣው “ልኀተ ጥበብ” ጋዜጣ በጥርና በየካቲት ወር 1998 ዓ. ም. እትሙ “በዘማሪዎቻችን አፍረናል” በሚል ርእስ በሰፊው መዘገቡ ይታወሳል፡፡
እኛም ይህንን በተመለከተ አንባብያን በጉዳዩ ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ እንዲያገኙ በማሰብ መዝሙር በማሳተምና በማከፋፈል የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውንም ሁለት አሳታሚዎች አነጋግረናል፡፡የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተውናል፡፡ መምህር ዘመድኩን ተክሌ የጌልጌላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት ባለቤት መዝሙር ቤቱ ሥራውን ከጀመረ 10 ዓመታት ሆኖታል፡፡ መዝሙር ቤቱ በአሳታሚነት ሥራና የመዝሙር ኦዲዮ ቪዲዮ ካሴቶችን ሲዲዎችን የማከፋፈል የማሠራጨት ሥራ እንደሚያከናውን መምህር ዘመድኩን ተክሌ ተናግረዋል፡፡

በኛ መዝሙር ቤት ለሚሠሩ ሥራዎች በተቻለ መጠን በጥንቃቄ ይደረጋል የሚሉት መምህር ዘመድኩን በኛ በኩል በሚደረገው ጥንቃቄ ብቻውን ግን ብዙም ለውጥ ማምጣት አይቻልም ይሆናል፡፡ በመዝሙር ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች እንዳሉ እሰማለሁ፡፡ ወደ ዘፈን የሚያዘነብሉ ጨርሶ ከዘፈን የተወሰዱ ዜማዎችም አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ሀብት አላት፡፡ አይደለም ከዘፈን ዜማ መቅዳት ቀድሞ ከተዘመረ መዝሙርስ ቢሆን ለምን ይገለበጣል? በማለት መምህር ዘመድኩን ሐሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ ቀጥለውም በራሳቸው በኩል ያለውን አሠራር ሲያስረዱ በምችለው መልኩ የማሳትመውን መዝሙር ለቤተ ክርስቲያን መምህራን አሳያለሁ፡፡ ነገር ግን ምንም ያህል ብጠነቀቅ ከግጥሙ ወይም ከዜማው ላይ ስሕተት ላይጠራ የይችላል ብለዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን በኩል እስካሁን ድረስ መዝሙርን በተመለከተ በወቅቱ ገምግሞ በሚገባ አርሞ መውጣት ባለበት ሰዓት የሚያስረክብ መዋቅር የለም፡፡ እንዲህ ዓይነት አሠራር ቢኖር ኖሮ አሁን የሚታዩት ችግሮች የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣የዶግማው፣ የትውፊቱ መጣስ ይቀንስ ነበር በማለት መፍትሔ የሚሉትን ሐሳብ ጠቁመዋል፡፡

ከመንፈሳዊ አግልግሎቱ በተጨማሪ የመዝሙር አሳታሚነት አገልግሎት የንግድ ሥራም እንደሆነ መምህር ዘመድኩን ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ በእኔ አሳታሚነት የሚወጣው መዝሙር በሁሉም ዘንድ የተወደደ እንጂ የሚነቅፍ እንዲሆን ፍላጎቱ የለኝም፡፡ ዘማሪውን ስመርጥና መዝሙርም ሲሠራ እኔ ተሳታፊ ነው የምሆነው፡፡ ሥራውን ለዘማሪው፣ ለግጥምና ዜማ ደራሲው፣ ለስቱዲዮና ለመሳሪያ ተጨዋቾቹ ብቻ አልተውም በማለት መምህር ዘመድኩን ስለ አሠራራቸውም አብራርተዋል፡፡ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከትምህርተ ሃይማኖት፣ ከታሪክ ከሌሎችም መመዘኛዎች አንጻር ክትትል አደርጋለሁ፡፡ ከኔ ውጪ ለሆኑ ሰዎችም የማሳይበት ሁኔታ አለ ይላሉ መምህር ዘመድኩን፡፡ ይህንን በተመለከተ አብረዋቸው መዝሙር የሰሩ ልጆች መመስከር እንደሚችሉ መምህረ ዘመድኩን ይናገራሉ፡፡
የመዝሙር ዜማና ግጥም አገኘሁ ብለውም መዝሙር እንደማያሳትሙ የጠቀሱት መምህር ዘመድኩን መዝሙር ካሳተሙ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው እንደሆነ አሰታውቀዋል፡፡ ባያሳትሙም እንኳን ለሥርጭት የሚመጡ መዝሙሮች ጉልህ ስሕተት ካለባቸው እንደማይቀበሉ ነው የሚናገሩት፡፡ መምህር ዘመድኩን በሥራቸው በኩል ያላቸውን እምነት ሲገልጹ፤ትችትም ወቀሳም ቢመጣ ሰበብ የማይደረደርበትን ተጠያቂነቱ በእርሳቸው ላይ እንዲያርፍ የሚፈልጉትን መዝሙር መሥራት እንደሚፈልጉ ይገልፃሉ፡፡

በመዝሙር ቤቶችና አሳታሚዎች በኩል ያለዉን ሁኔታም መምህር ዘመድኩን ሲገልጹ፤ምክንያቶች ከራሳችን ድክመት በተነሣ ይሁን በሌላ በመካከላችን ሠፊ ክፍተት ነው ያለው፡፡ በግልጽ ለመናገር የሚያስደፍረው ግን የተገኘውን አጋጣሚተጠቅሞ አንዱ አንደኛውን ለመቅበር የሚደረግ ሩጫ ይታያል፡፡ የመዝሙር አሳታሚነት አከፋፋይነት አገልግሎት ደግሞ ከሌላው የንግድ ሥራ ለየት ያለ ነው፡፡ የሚሉት መምህር ዘመድኩን፤ ሥራው የካደ የሚመለስበት፣ ያዘነ የሚጽናናበት፣ በኃጢአት የሚኖር ሰው በንስሐ እንዲመለስ የሚያደርግ ሥራ ነው የምንሠራው፡፡ በሥራው ውድድር ቢኖርም ሥርዓት የጠበቀ ባለመሆኑ በአንድ ቀን ወይም በተወሰኑ ቀናቶች መካከል በርካታ የመዝሙር ካሴቶች ገበያ ላይ የሚውሉበት አጋጣሚዎችን አስተውለናል፡፡ይሄ ዘማሪውንም አሳታሚውንም አድማጩንም የሚጠቅም አካሄድ አለመሆኑን መምህር ዘመድኩን ያስገነዝባሉ፡፡

በመዝሙር ቤቶች መካከል ግልጽ አሠራር የለም፡፡ ሁሉም በምሥጢር ነው የሚሠራው፡፡ በንጹሕ መንፈስ ለመልካም ሥራና ውጤት የሚያበቃ ቀና ግንኙነት የለም፡፡ ዛሬ ምን እየተሠራ ነው? ማን ጋ ነው የሚሠራው? መባባል አልተለመደም፡፡ ተገናኝቶ ተቀራርቦ መነጋገር፣ ምን እናድርግ ሥራው የጋራ ነው የሚል ዕድል ተሰምቶ አያውቅም፡፡ ይላሉ መምህር ዘመድኩን፡፡

መዝሙሮች ደረጃቸውን የጠበቁ እነዲሆኑና ከችግር እንዲጸዱ በቤተ ክርስቲያኗ ዕውቅናና ሥርዓት መወሠረት ለመታተማቸው ማረጋገጫ እንዲያገኙ መፍትሔው ራሱን የቻለ ይህንን ጉዳይ የሚከታተል ክፍል በቤተ ክርስቲያን ሥር ማቋቋም ነው፡፡ የሚሉት መምህር ዘመድኩን፤ የሚቋቋመው ማዕከል በደንብ የተደራጀ፣ በጊዜ ከማየት እና በሚገባ ከመገምገም አንስቶ ከቤተ ክርስቲያኒቷ ትምህርት ሥርዓት ዕውቀት አንጻር የማይታማ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሥራዎችን ተረክቦ የሚያጓትት ከሆነ ግን መልሶ ችግር ፈጣሪ ሊሆን እንደሚችል መምህር ዘመድኩን ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

መዝሙር ስብከተ ወንጌል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ አገልግሎት ትኩረት ልትሰጠው ይገባል ይላሉ መምህር ዘመድኩን፡፡ የአድማጩ ቁጥር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጣም ጨምሯል፡፡ ለዚህ ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ጥናት የሚፈልግ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን በየታክሲው በየሬስቶራንቱ በየትኛውም ቦታ መዝሙር ሲደመጥ ይታያል፡፡ በርግጥ ይላሉ መምህር ዘመድኩን ምእመናን ዝም ብለው ያገኙትን ሁሉ አይገዙም፡፡ አይተው መዝነው አንገዋለው የሚተውበት ሁኔታ አለ፡፡ እንዲያውም መዝሙር ከተቀረጸ በካሴት ከወጣ በኋላ ሆነ እንጂ ምእመናን ናቸው መዝነው ከገበያ ውጪ የሚያደርጉት፡፡ በማለት መምህር ዘመድኩን ያስረዳሉ፡፡

ቀደም ስል ቢቋቋም ብዬ የጠቀስኩት የቁጥጥሩን ፣የክትትሉን ሥራ የሚሠራ ክፍል ወይም ማዕከል ባለመኖሩ ብዙ ችግር ነው የሚያጋጥመን፡፡ የሕጋዊነት ጥያቄም ይኖራል፡፡ የሚሉት መምህር ዘመድኩን፣ እርሳቸው በሚያሳትሟቸው መዝሙራት ላይ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እምነት የተዘጋጀ” የሚል መግለጫ እንደማይለጥፉባቸው ግልጸዋል፡፡ ለዚህ ምክንያት እንዳላቸውም እንዲህ በማለት ይጠቅሳሉ፡፡ የማሳትማቸው መዝሙሮች በራሴ በኩል ለቤተ ክርስቲያን መምህራን ባሳይም ከሚመለከተው የቤተ ክርስቲያን አካል ወይም ክፍል /ክፈሉ ባይኖርመ/ በቤተ ክርስቲያኗ እምነትና ሥርዓት መሠረት ለመዘጋጀቱ ሕጋዊ ማስረጃ ባለ ማግኘቴ ነው፡፡ ይሄ እምነቴ በመሆኑ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ ያለው አማራጭ በዚሁ መቀጠል ብቻ ይሆናል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በብዛት የሚሰሙትን መዝሙሮች በተመለከተ መምህር ዘመድኩን ሲገልጹ፤ በአብዛኛው ተለዋዋጭ ነው ምክንያቱም አድማጩ ስለሚለያይ ነው፡፡ ዜማዎቹ ግጥሞቹ ወሳኝ ናቸው፡፡ ጥሩ ዜማ ኖሮአቸው ወደንስሐ የሚያዘነብሉ መዝሙሮች አድማጭ አላቸው፡፡ በአጠቃላይ ግን ወቅቱ ይወስነዋል፡፡ ዘመኑን የሚዋጁ መዝሙራት ሰፊ ቦታ ይይዛሉ፡፡ የህዝቡን ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ገጽታዎችን ከዳሰሰ፣ ልብን የሚነካ በምንፈስ ከእግዚአብሔር ነእና ከቅዱሳኑ ጋር የሚያገናኝ ከሆነ ሁሉም ሰው ያዳምጠዋል በማት መምህር ዘመድኩን ያስገነዝባሉ፡፡

በመዝሙር ዙሪያ ለተፈጠሩ ጉድለቶች አሳታሚው፣ ዘማሪው፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ጽዋ ማኀበራት፣ ምእመናን፣ መምህራን፣ የዜማና ግጥም ደራሲዎች፣ ማኀበረ ቅዱሳን፣ ሌሎችም መንፈሳዊ ማኀበራት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ልዩነቱ ደረጃው ነው እንጂ ሁሉም ድርሻ ድርሻ አላቸው እየደረሰ ላለው ጉድለት የአንበሳውን ድርሻ ማን ይወስዳል? ምርምር የሚያስፈልገው ነው፡፡ ይላሉ መምህር ዘመድኩን ተክሌ ስለዚህ አንዱ ወገን ላይ ብቻ ጉድለቱን ማሳረፍ አይቻልም፡፡

በድምጽ ማጉያ በየቦታው በተለይም በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ዙሪያ መዝሙርን ማስተዋወቅን በተመለከተ ስንናገር መነሻዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያውን ምክንያት መምሀር ዘመድኩን ሲገልጹ፤ መዝሙር በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የሚተዋወቅበት ለአድማጩ ጆሮ እንዲደርስ የሚነገርበት ምንም ዕድል የለም፡፡ ዘፈንን አሰመልክቶ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያ ይነገርላቸዋል፡፡ ዓለማዊው ነገር ከመዝሙር በተሸለ የሚተዋወቅበት ዕድል እንዳለው መምህር ዘመድኩን ያስገነዝባሉ፡፡ መንግሥት ለዘፈንም ለመዝሙርም አሳታሚዎች የሰጠው ፈቃድ አንድ ዓይነት ነው፡፡ ለኛም ለእነርሱም “የኤሌክትሮኒክስ አሳታሚዎች” የሚል ፈቃድ ነው የተሰጠው፡፡ መዝሙር በመንግሥት የአሠራር ፖሊሲ የተነሳ መገናኛ ብዙኃኑ የመዝሙር ማስታወቂያ አይሠሩልንም በማለት መዝሙር አሳታሚዎች ገጠማቸውን ችግር ያስረዳሉ፡፡

አንዳንድ ምእመናን መዝሙርን ማስተዋወቅ አያስፈልግም፡፡ ጥሩ መዘሙር ከሆነ ያለማስተወቂያ ይሸጣል ይደመጣል ይላሉ፡፡ በማለት ለቀረበው ሐሳብ “ይሄ ችግር ያለበት አመለካከት ነው፡፡ የሚተዋወቅበት መስመር መጥበቡ ነው እንጂ ማስታወቂያ /ቷደቨጵረተፀሰመጵነተ/ አሁን ባለው የሰለጠነ ዘመን ገበያ መር ኢኮኖሚ /የኛ ሥራ መንፈሳዊ አገልግሎት መሆኑ ሳይረሳ ከንግድ ጋር አገጣጥሞ/ አማራጭ የሌለው የገበያ አምጭ ዘዴ ነው፡፡ በኛ የሥራ ልምድ ብዙ ያስተዋልነው ነገር አለ፡፡ መዝሙር ቤት ሔዶ የመግዛት ነገር ብዙም አልነበረም፡፡ በየቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ የመዝሙር ካሴት ይዘው የምናያቸው አዟሪዎች እኮ በዚያ የሚቆሙበት ምክንያት ምእመኑ ተምሮ ሲወጣ ገዝቷቸው እንደሚሔድ ስለሚያውቁ ነው፡፡ ይላሉ መመህር ዘመድኩን፡፡ ስለዚህ ጠቅለል አድርጎ ለማስቀመጥ አሳታሚዎችን ወደ አደባባይ ያወጣን የሰውንም ጆሮ እንድናደነቁር ያደረገን ይሄ ችግር ነው፡፡

ይሄ ብዙ ጉዳት እንዳለው እንገነዘባለን የሚሉት መምህር ዘመድኩን ይሄን ሥራ የጀመርነውም ሰዎች ሳይሰማን ቀርቶ አይደለም፡፡ እኔ ራሴ በሆነው ነገር አፍርበታለሁ፡፡ በወቅቱ ስጀምረው ግን ምንም አልተሰማኝም ነበር፡፡ ችግራችንን እናቃልልበታለን ብለን የጀመርነው ነገር አሁን የባሰ ችግር ሊፈጥር ይችላል እየፈጠረም ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት አዲስ አበባ የካ ሚካኤል የሀነውን ማንሣት ይቻላል፡፡ በዚያች ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ በሚያሰገባ ቀጭን መንገድ ከ9 በላይ የሆነ እጅግ ከፍተኛ ኃይል ያለው ድምጽ ማጉያ ከግራና ከቀኝ ሲጮህ ለጸሎትና ለትምህርት የመጣው ሰው ሊሆን የሚችለውን ማሰብ ይቻላል፡፡ ጥሩ ነው ብለን ብንቀበለው እንኳ ከጤና አኳያ በጆሮ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በቀላሉ የሚታይ ይሆናል? ለዚህ ምን ምላሽ መስጠት እንሚቻል አላውቅም፡፡ ችግሩ ግን በወቅቱ እንዲህ እንድናደርግ አስገድዶን ነበር፡፡ ይላሉ መምሀር ዘመድኩን፡፡

በድምጽ ማጉ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚሠራውን የማስተዋወቅ ሥራ አሁን ሳየው ችግር እንዳስከተለ ይገባኝል፡፡ የሚሉት መምህር ዘመድኩን በምንም መልኩ ይደገፋል የሚል ሐሳብ የለኝም፡፡ ይሄን የምለው ተጎጂ እየሆንኩ ነው፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን እውነቱን ስንነጋገር ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ የሰላም የጽሞና ደጃፍ ነች እንጂ የሁከት አደባባይ አይደለችም፡፡ አስከዛሬ እንዲህ ያደረግነው ግን ወደን አይደለም፡፡ በራሴ በኩል ግን ጉዳዩ የተወሳሰበ ቢሆንም በድምጽ ማጉያ ማስተዋወቁን አቁሜያለሁ፡፡ በማለት መምህር ዘመድኩን ያስረዳሉ፡፡ ሌሎች አሳታሚዎች ቢጠየቁ የሚደረገው ነገር አሠራሩ ጥሩ ነው፡፡ በዚሁ ይቀጥል የሚሉ አይመስለኝም ብለዋል፡፡

አንድ ስማቸው እነዲጠቀስ ያልፈለጉ የመዝሙር ካሴት አሳታሚ በወቅቱ የሚታተሙ መዝሙራትን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት አንዳንድ ዘማርያን የዘፈን ዜማዎችን ለመዝሙር በመለወጥ ወይም ወደ ዘፈን ዜማ በሚያጋድል ዜማ የሚዘመርበት አጋጣሚ አለ፡፡ በእኛ መዝሙር ቤት አንድ ዘማሪ መጥቶ የመዝሙር ካሴት ለማሳተም እንድንዋዋል ሲጠይቅ በቅድሚያ መዝሙሩን እንመለከተዋለን፡፡ ኦሮቶዶክሳዊ ሥርዓትን መከተሉን የዘማሪውን ማንነት፣ ዜማውን፣ ግጥሙን በተቻለ ለማጣራት እንሞክራለን፡፡ እንዲሁም ለሊቃውንት አባቶች እናሳያለን፡፡ አባቶች አይተውት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ ከሆነ ወደ ሥራ ቀይረነው በገበያ ላይ እናውለዋለን፡፡

በመዝሙሮች ላይ ዜማ ወደ ዘፈን ያጋደለ እንዲሆን ፍላጎት የለንም መደረግም የለበትም፡፡ እስከ አሁን ድረስ በእኛ መዝሙር ቤት ከዘፈን ጋር ተቀራራቢ የሆኑ ዜማዎችን ይዘው የሚመጡ አዘማርያን ይኖራሉ፡፡ የኛ መዝሙር ቤት በሚያሳትማቸው መዝሙራት እሳካሁን አስተያየት ተሰጥቶ አያውቅም፡፡ ለዚህ ችግር መፈጠር ምክንያት የሚመስለኝ አንዳንድ ዘማሪያን ግጥሙን፣ ዜማውን ሳያስገመግሙ በዚያው ወደ አድማጭ ይለቃሉ፡፡ አሳታሚውም ለዚህ ትኩረት ባለመስጠት ስሕተቱን ይደግሙበታል፡፡ በዚህ የተነሳ የዚህ ዓይነቱ ችግር ሊከሰት የሚችል መሆኑን እኚሁ አሳታሚ ያስረዳሉ፡፡

አሳታሚው በቪሲዲ የሚዘጋጁ መዝሙራትን በተመለከተም አስተያት አላቸው፡፡ መዝሙርን በቪሲዲ ማዘጋጀት ከተጀመረ አንድ ሦስት ዓመት ይሆነዋል፤ በቪሲዲው ብዙ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት አለ፡፡ ሁል ጊዜ በቪሲዲ ሸብሸቦ ብቻ ነው የሚታየው፣ አንዳንድ ሰዎች የቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዓተ የጠበቀ ከሆነ በስክሪፕት ለምን አትሠሩም የሚል ሐሳብ ያላቸው አሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ አሁን “ስንፔር” የተባለው ረቂቁ /ስክሪፕቱ/ ተጽፎ ነው የተሰራው፡፡ ሥራው ግን ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ውጪ የሆነ ነገር ይታይበታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥሩ ሥራ የሚሠሩም አሉ፡፡ በርግጥ ረቂቅ ጽሑፍ /ስክሪፕት/ ሲጻፍ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ ሕዝቡ ለውት ይፈልጋል፡፡ ሁሌ አኝድ ዓይነት ነገር ማየት የለብንም ነው የሚለው፡፡ ሆኖም ግን ሕዝቡ እንዲህ ይላል ተብሎ የተለየ ጽሑፍ ተዘግጅቶ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ሆኖ መሠራት የለበትም በማለት ተናገረዋል፡፡

አንድ ቪሲዲ ወይም የመዝሙር ካሴት ተዘጋጅቶ ለሕዝቡ ሲቀርብ ችግር ቢኖረውም ተጠያቂው ዘማሪውም አሳታሚው መዝሙር ቤቱም ናቸው፡፡ መዝሙር ቤቱ ዜማው፣ ግጥሙ እንዲህ ይሁን ገበያ እንዳገኝ ይሄ ነገር ይግባልኝ ማለት የለበትም፡፡ ዘማሪውም መዝሙር እንዲሸጥልኝ ይሄ ይሁንልኝ እዚህ ጋር ይሄ መግባት አለበት ማለት የለበትም፡፡ ሁለቱም የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዓት በጠበቀ መንገድ ሕዝቡን የሚያንጽ ነገር ነው ማዘጋጀት ያለባቸው፡፡ ሊደረግ የሚገባውም ይሄ ነው፡፡ አንድ ቪሲዲ በሚወጣበት ጊዜ ዘማሪውና አሳታሚው ቁጭ ብለው መከታተል አለባቸው፡፡ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በአባቶች፣ በባለሙያ አሳይተው ማውጣት አለባቸው ይሄ ሐላፊነት የሁለቱም ነው፡፡

አንድ መጽሐፍ፣ ዌም መዝሙር አርሙልን ተብሎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቢገባ ያንን ለማረም ዓመትና ከዚያም በላይ ሊወስድ ይችላል፡፡ ዓመት ጠብቀን የምንሠራ ከሆነ ሥራ መሥራት ኤቻልም፡፡ አግልግሎቱም ወደ ኋላ ይጎተታል፡፡ እኔ እንደማምነው ይሄ አገልግሎት በመጀመሪያ ደረጃ ለነፍስ ነው ሁለተኛ ለሥጋ ነው፡፡ ዘማሪያን፣ ግጥም ገጣሚዎች፣ ዜማ ደራሲዎች በነፃ አይሠሩም የተወሰነ ጥቅም ያገኙበታል፡፡

ስለዚህ ቤተክህነት ህንኑ የሚከታተል አንድ አካል አቋቁማ የካሴቶች የቪሲዲዎችን አገልግሎት ይዛ ሥራዎችን እያየች እየመረመረች ብታሳልፍ ሁሉን ነገር ብትቆጣጠር ደስተኞች ነን፡፡ እኛም ጉዳዩ በወቅቱ በሚገባ የሚፈጸም ከሆነ ለማሳረም ወደዛ ይዘን እንሄዳለን፡፡ እንዲህ የማይሠራ ከሆነ በደፈናው ዝም ብሎ ተቃውሞ ከሆነ የሚሆን ነገር አይደለም፡፡

አንድ ዘማሪ በስሜት ተነሣሥቶ ዝም ብሎ ገንዘብ ለማግኘት ሲል እዘምራለሁ ቢል ላይሆን ይችላል፡፡ እኔ የማምነው ሁሉም በጸጋው መስበክ የሚገባው ቢሰብክ፣ መዘመር የሚገባው ቢዘምር ጥሩ ነው፡፡ እንዲሁ ብቻ ተነሥቶ ሰዎች ስላወጡ በማለት ቢያሳትም ራሱን ይጎዳል፡፡ጸጋው ከሆነ ሰዎች ይታነጹበታል ራሱ ይጠቀምበታል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ዘማሪ በጸጋው ቢጓዝ መልካም ነው ብለዋል፡፡

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት እኝህ የመዝሙር አሳታሚ ስለ ማስታወቂያም የሚሉት አላቸው፡፡ አንድ የመዝሙር ቪሲዲ፣ መጽሔት፣ መጽሐፍ ማንኛውም ለምእመናን የሚጠቅም ነገር ሲታተም ማስታወቂያ መሠራት መቻል አለበት የሚል እምነት አላቸው፡፡ በዚህ ሥራ ላይ ሳናውቅ ለብዙ ዓመታት ተጎድተንበታል፡፡ ከዛሬ 13 ዓመት በፊት በሬዲዮና በቴሌቪዥን መንፈሳዊ የሆኑ ነገሮችን ማስተዋወቅ ይቻል እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ አሁን ግን ቆሟል፡፡ በዛ ብናስተዋውቅ ኖሮ ምእመናን አዳዲስ ነገሮች መውጣታቸውን ስለሚያውቁ ካሴቱን ይገዙ ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዐት በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያ መሥራት አይቻልም፡፡ እኔ ለብዙ ጊዜ በድምጽ ማጉÃ
October 2008
SMTWTFS
September 2008November 2008
1234
567891011
12131415161718
19202122232425
262728293031