ከአዳም ነው ግኝትህ
Sunday, 21. September 2008, 20:57:20
ከአዳም ነው ግኝትህ
ዘፍ 1፡ 26- 28
ብዙ አውቀናል ስንል ብዙ ተምረናል፣
የጎደለን አለ ገና ይቀረናል፡፡
አንድ የመሆን ነገር እንደ ሻማ ቀልጦ፣
መስማማት ከበደን ከፍቅር ዘር በልጦ፡፡
ብዙና ተባዙ ምድርን ሙሏት ማለት፣
ተዋጉ አልነበረም ይህን እወቅ ፍጥረት፡፡
በሰናኦር ምድር ቋንቋ ቢደባለቅ፣
“ባቢሎን” ተብሎ ከተማ ቢታወቅ፣
ምድሪቱን ቢሞላት ህዝብ ተበትኖ፣
ሃገር ቢከፋፈል ድንበር ተወስኖ፣
ለምን ነው መንደዱ የጸብ የጥል እሳት፣
የሰው ልጅ ለማጥፋት ጦር መምዘዝ ጦር ማንሳት፡፡
ምነው ያዜብ ንግስት ከጦቢያ ተነስታ፣
ሰላም ይዛ መጣች እውቀት ጥበብ አይታ፡፡
የጀግና ዘር ብለህ አትታጠቅ ዝናር፣
መግደል ውርስ አይሆንም እባክህ ሰው ተማር፡፡
ባለንበት ዘመን ጀግንነት ወንድነት፣
ተስማምቶ መኖር ነው በፍቅር ባንድነት፡፡
የሰው ልጅ ከማዳን የሰው ልጅ ለማጥፋት፣
ስንት ጥበበኛ ይጫወታል በእሳት፡፡
ሰው ጥበብ እውቀትህ ችሎታህ ሲለካ፣
ሃብት ያፈሰስክበት ለጥይት ነው ለካ፡፡
በደቂቃ የሚገል መሳሪያ ሲሰራ፣
በደቂቃ የሚድን ምነው አልተሰራ?
ባልተገባ ነገር በማይሆን ተጣልተን፣
አብረን እየበላን ሆድና ጀርባ ነን፡፡
መንገድ ሊያሳስተን ሊያጣላን ከመሲህ፣
ሰይጣን እባብ ሆኖ አይመጣም ከእንግዲህ፡፡
ስንፍናችን ታውቆ ለዘር ማደራችን፣
ሰይጣን ተደላድሎ ገባ መሃላችን፡፡
ሁሉ ፍጡር ሆኖ አምላክ የቀረፀው፣
ነገድ ጎሳ ከፍለህ ምነው ተጣላህ ሰው፡፡
“የእገሌ ! የእገሌ ! “ ሲባባሉ ሰምቶ፣
ሰውን ተከትለው ሲከፋፈሉ አይቶ፣
ሐዋርያ የሚሆን የጌታ ክርስቶስ፣
ይህን ተናገረ እንዲህ አለ ጳውሎስ፡፡
“የ አጵሎስ ነኝ ትላለህ አጵሎስ ምን አረገ፣
የጳውሎስ ነኝ ትላለህ ጳውሎስ ምን አረገ፣
ሰው ቢወጣ ቢወርድ ልቡ እንደፈለገ፣
እግዚአብሔር አይደል ወይ ተክሎ ያሳደገ? “
የተወለድክበት ስፍራው ቢነገርህ፣
የሰው ልጅ መሞቻህ አይደል እንዳሳብህ፡፡
ለመቀራረቡ አብሮ ለመብላቱ፣
“ ሰሜን ደቡብ” መባል ባልከፋ ሰርአቱ፡፡
“ምስራቅ ምዕራብ” ብሎ ለጦር መደራደር፣
ያ ነው ግብዝነት መንገድ ስቶ ማደር፡፡
እንግዳ እየሆነ ሚስጥር አይክበድህ፣
ሐቁን ስማ ፍጥረት እውነት ይኸውልህ፣
በአንተ “ሰሜን” መሆን በአንተ ”ደቡብነት”፣
በአንተ “ምስራቅ” መሆን በአንተ “ምዕራብነት”፣
ምን ይገኛል ብለህ ነገድ ከፋፈልህ፣
የስድስተኛ ቀን የእግዚአብሔር ፍጡር ነህ፡፡
እራስክን ከፍ አታድርግ ከማንም አትበልጥም፣
እራስክን ከፍ አታድርግ ከማንም አታንስም፣
አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም፡፡
ከ አዳም የተለየ የዘር ግንድ የለህም፡፡
ሰው አንተን ባይመስል ይዘት ቅርፅ አቋም፣
አይን ጥርስ አፍንጫ ጠጉርና ቀለም፣
የጥቁር የነጩ የ ቀይ የጠይሙ፣
እንደ መልኩ አይደለም አንድ አይነት ነው ደሙ፡፡
ወዶ ቀይ አልሆነም ፈልጎ አልጠቆረም፣
ይኸን መርጦ አመጣው እግዚአብሔር ወደ ዓለም፡፡
አንተ አዘኸው አይደል የሰው ጠይምነት፣
እግዚአብሔር ፈቅዶ ነው የመልክን ልዩነት፡፡
ከየት እንደመጣህ ማስተዋል አትርሳ፣
ምነው ዘር ከመሃል ትቆጥራለህሳ?
ከሰሜን አይደለም ትውልድ አመጣጥህ፣
ከደቡብ አይደለም የዘር መሠረትህ፣
ከምስራቅ አይደለም ጎሳና ነገድህ፣
ከምዕራብ አይደለም የሰው ልጅ እርስትህ፣
መነሻ መፍለቂያ የሕይወት ጅምርህ፣
ካፈር ከተሰራው ከአዳም ነው ግኝትህ፡፡
ሰው ክቡር ነህና ማስተዋል ይብዛልህ፣
የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡
ያቺን ቀን በጸፍ ጸፍ
/ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ/
በአብረሃም ሰሎሞን
ዘፍ 1፡ 26- 28
ብዙ አውቀናል ስንል ብዙ ተምረናል፣
የጎደለን አለ ገና ይቀረናል፡፡
አንድ የመሆን ነገር እንደ ሻማ ቀልጦ፣
መስማማት ከበደን ከፍቅር ዘር በልጦ፡፡
ብዙና ተባዙ ምድርን ሙሏት ማለት፣
ተዋጉ አልነበረም ይህን እወቅ ፍጥረት፡፡
በሰናኦር ምድር ቋንቋ ቢደባለቅ፣
“ባቢሎን” ተብሎ ከተማ ቢታወቅ፣
ምድሪቱን ቢሞላት ህዝብ ተበትኖ፣
ሃገር ቢከፋፈል ድንበር ተወስኖ፣
ለምን ነው መንደዱ የጸብ የጥል እሳት፣
የሰው ልጅ ለማጥፋት ጦር መምዘዝ ጦር ማንሳት፡፡
ምነው ያዜብ ንግስት ከጦቢያ ተነስታ፣
ሰላም ይዛ መጣች እውቀት ጥበብ አይታ፡፡
የጀግና ዘር ብለህ አትታጠቅ ዝናር፣
መግደል ውርስ አይሆንም እባክህ ሰው ተማር፡፡
ባለንበት ዘመን ጀግንነት ወንድነት፣
ተስማምቶ መኖር ነው በፍቅር ባንድነት፡፡
የሰው ልጅ ከማዳን የሰው ልጅ ለማጥፋት፣
ስንት ጥበበኛ ይጫወታል በእሳት፡፡
ሰው ጥበብ እውቀትህ ችሎታህ ሲለካ፣
ሃብት ያፈሰስክበት ለጥይት ነው ለካ፡፡
በደቂቃ የሚገል መሳሪያ ሲሰራ፣
በደቂቃ የሚድን ምነው አልተሰራ?
ባልተገባ ነገር በማይሆን ተጣልተን፣
አብረን እየበላን ሆድና ጀርባ ነን፡፡
መንገድ ሊያሳስተን ሊያጣላን ከመሲህ፣
ሰይጣን እባብ ሆኖ አይመጣም ከእንግዲህ፡፡
ስንፍናችን ታውቆ ለዘር ማደራችን፣
ሰይጣን ተደላድሎ ገባ መሃላችን፡፡
ሁሉ ፍጡር ሆኖ አምላክ የቀረፀው፣
ነገድ ጎሳ ከፍለህ ምነው ተጣላህ ሰው፡፡
“የእገሌ ! የእገሌ ! “ ሲባባሉ ሰምቶ፣
ሰውን ተከትለው ሲከፋፈሉ አይቶ፣
ሐዋርያ የሚሆን የጌታ ክርስቶስ፣
ይህን ተናገረ እንዲህ አለ ጳውሎስ፡፡
“የ አጵሎስ ነኝ ትላለህ አጵሎስ ምን አረገ፣
የጳውሎስ ነኝ ትላለህ ጳውሎስ ምን አረገ፣
ሰው ቢወጣ ቢወርድ ልቡ እንደፈለገ፣
እግዚአብሔር አይደል ወይ ተክሎ ያሳደገ? “
የተወለድክበት ስፍራው ቢነገርህ፣
የሰው ልጅ መሞቻህ አይደል እንዳሳብህ፡፡
ለመቀራረቡ አብሮ ለመብላቱ፣
“ ሰሜን ደቡብ” መባል ባልከፋ ሰርአቱ፡፡
“ምስራቅ ምዕራብ” ብሎ ለጦር መደራደር፣
ያ ነው ግብዝነት መንገድ ስቶ ማደር፡፡
እንግዳ እየሆነ ሚስጥር አይክበድህ፣
ሐቁን ስማ ፍጥረት እውነት ይኸውልህ፣
በአንተ “ሰሜን” መሆን በአንተ ”ደቡብነት”፣
በአንተ “ምስራቅ” መሆን በአንተ “ምዕራብነት”፣
ምን ይገኛል ብለህ ነገድ ከፋፈልህ፣
የስድስተኛ ቀን የእግዚአብሔር ፍጡር ነህ፡፡
እራስክን ከፍ አታድርግ ከማንም አትበልጥም፣
እራስክን ከፍ አታድርግ ከማንም አታንስም፣
አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም፡፡
ከ አዳም የተለየ የዘር ግንድ የለህም፡፡
ሰው አንተን ባይመስል ይዘት ቅርፅ አቋም፣
አይን ጥርስ አፍንጫ ጠጉርና ቀለም፣
የጥቁር የነጩ የ ቀይ የጠይሙ፣
እንደ መልኩ አይደለም አንድ አይነት ነው ደሙ፡፡
ወዶ ቀይ አልሆነም ፈልጎ አልጠቆረም፣
ይኸን መርጦ አመጣው እግዚአብሔር ወደ ዓለም፡፡
አንተ አዘኸው አይደል የሰው ጠይምነት፣
እግዚአብሔር ፈቅዶ ነው የመልክን ልዩነት፡፡
ከየት እንደመጣህ ማስተዋል አትርሳ፣
ምነው ዘር ከመሃል ትቆጥራለህሳ?
ከሰሜን አይደለም ትውልድ አመጣጥህ፣
ከደቡብ አይደለም የዘር መሠረትህ፣
ከምስራቅ አይደለም ጎሳና ነገድህ፣
ከምዕራብ አይደለም የሰው ልጅ እርስትህ፣
መነሻ መፍለቂያ የሕይወት ጅምርህ፣
ካፈር ከተሰራው ከአዳም ነው ግኝትህ፡፡
ሰው ክቡር ነህና ማስተዋል ይብዛልህ፣
የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡
ያቺን ቀን በጸፍ ጸፍ
/ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ/
በአብረሃም ሰሎሞን
ከአዳም ነው ግኝትህ

